Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Work Hours
Monday to Friday: 7AM - 7PM
Weekend: 10AM - 5PM
Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Work Hours
Monday to Friday: 7AM - 7PM
Weekend: 10AM - 5PM

የሁለቱ የጉራጌ ዞን አስተዳደሮች፣ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር እና የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በጋራ ያዘጋጁት የጉራጌ ታሪክ፣ ባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ዩኒቨርቲው ከመማር ማስተማር ስራው ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ የማህበረሰብ አገልግሎት የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመስራት የህብረተሰቡን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ካለበት አካባቢ አንፃር የጉራጌ ህዝብ ቋንቋ፣ባህልና ታሪክ እንዲጎለብት ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛልም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
ከዚያ ቀደም የተከናወኑ ተግባራት እንዳሉ ሆነው በተለይም ሃገር በቀል እውቀቶች ባህል፣ቋንቋና ታሪክ ላይ መስራት መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ በዘርፉ ስትራቴጂክ እቅድ ነድፎ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንዳለም አመላክተዋል ።
በባህሉ ዘርፍም እንዲሁ እየተረሱ የነበሩና እየተሸረሸሩ የመጡትን እንዲያንሰራሩና ዳብረው እንዲዎጡ የማድረግ ስራም ተሰርቷል ብለዋል በንግግራቸው።
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቅባቱ ተሰማ በጉራጌ የታሪክ የቋንቋና የባህል ስራዎች ላይ ከጉራጌ ዞኖች አስተዳደሮች ከወልቂጤና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲዎች ጋር በመተባበር እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል።
በዚህም በታሪክ በቋንቋና በባህል ዘርፎች ላይ ከተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በተለይም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጉራጌ የታሪክ፣ የባህልና የቋንቋ የጥናት ዶክመንቶችን በማጠናቀቅ አሁን ላይ ወደ ጆርናል ደረጃ መድረሳቸውንም አክለዋል።
እነዚህን ስራዎች ማህበረሰቡ ጋር ለማድረስ የህትመት ስራ ለማሰራት ማህበሩ በዝግጅት ላይ መሆኑንም አንስተዋል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቅባቱ ።
በተጨማሪም የጉራጌ ብሄረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስርአቶች ተሰንደው ማገልገል እንዲችሉ ከየአካባቢው ባህል ሽማግሌዎች ጋር በመሆን እነዚህን የጥናት ውጤቶች ተጠናቀው ወደ ህትመት እየሄዱ ነውም ብለዋል አቶ ቅባቱ ተሰማ።





