የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው የጉራጌ ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚየም ኤግዚብሽን በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ መርቀው ከፈቱ።

የጉራጌ የታሪክ፣ የቋንቋና የባህል ሲንፖዚየም በወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት በመካሄድ ላይ ነው።

የጉራጌ ማህበረሰብ ለዘመናት ሲገለገልባቸው የቆዩ ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶችና ቅርሶች እንዳለው ይታወቃል።

በኤግዚብሽኑም የጉራጌ ባህላዊ ምግቦች፣ የእደጥበብ ስራዎች ፣ አልባሳቶች፣ ፎቶ ጋላሪዎችና ሌሎችም ማህበረሰቡን የሚገልጹ ልዩ ልዩ ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶች ቀርበዋል።

እነዚህ ባህላዊ ቁሳቁሶችና ቅርሶችን ተጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገሩ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይጠበቅበታል መልዕክታችን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *