አንድነትን ይበልጥ በማጠናከርና የጋራ እሳቤ በመያዝ የጉራጌ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ፦የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን

የጉራጌ የባህል ፣ የቋንቋና የታሪክ ሲፖዚየም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በማጠቃለያ ሀሳባቸው እንደተናገሩት አንድነትን በማጠናከርና የጋራ እሳቤ በመያዝ የጉራጌ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ጉራጌ የራሱ የሆነ ባህል ፣ቋንቋ ፣ታሪክ እና ቅርስ ባለቤት እና በሌሎች መስተጋብሮቹም አኩሪ እሴት ያለው ማህበረሰብ ስለመሆኑ አንስተዋል።

አቶ ሙስጠፋ አክለውም የጉራጊኛ ቋንቋ እንዲለማ በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸው አንስተው በቀጣይም በዘርፉ ሰፋፊ የሚሰሩ ተግባራት እንዳሉ አመላክተዋል።

በአንድ አካባቢ የታዩ ጅምር ስራዎች በሁሉም አካባቢ በማስፋት ፣ ወንድማማችነትና እህተማማችነት በማጠናከር

የጉራጌ አንድነት እና አብሮነት ይበልጥ እንዲጎለብት በትኩረት እንስራለን ሲሉ አቶ ሙስጠፋ አስታውቀዋል።

ሲፖዚየሙ በቀጣይ ከፍ ባለደረጃ ለማካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አስፈላጊውን ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለሲፖዚየሙ መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትም ምስጋናቸው አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *