የጉራጌ ህዝብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ተዋዶና እና ተፋቅሮ የመኖር ባህሉን ይበልጥ እያጎለበተ ሊሄድ ይገባል ሲሉ በየጉራጌ ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚም የታደሙ ሳታፊዎች ተናገሩ።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት (ዶ/ር) ፋሪስ ደሊል ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው የጉራጌን ባህል እና ቋንቋ በማሳደግ ረገድ የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

ቋንቋና ባህል ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ትልቅ እሴት እንደመሆኑ መጠን በጥናትና ምርምር ስራዎች ማስደገፍ የግድ የሚል ጉዳይ ነው።

የጉራጌ ህዝብ በሁሉም ሀገሪቱ ክፍል ተዋደው እና ተፋቅረው የሚኖር ህዝብ በመሆኑ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶች የበለጠ ማጉላት ከምሁራን ይጠበቃል ሲሉ ዶ/ር ፋሪስ ተናግረዋል።

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስተያየት ከሰጡት መካካል አቶ በለጠ ወልዴ እንደገለፁት የተደረገው ሲምፖዚየም የጉራጌን ህዝብ ታሪክ፣ ቋንቋ እና ባህልን ለዓለም ህዝብ የማስተዋወቅ ዓላማን የያዘ ነው ብለዋል።

ቱባ ባህልን ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ የባህል ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ ስለመሆኑም ተናግረው ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም የህዝቡን ድንቅ ባህልና ቋንቋ ከማስተዋወቅ ረገድ የድርሻውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወ/ሮ ፈሰሰወርቅ ገ/ሰንበት የጋራ እሴቶችን በማጉላት ቱባ ባህሎችን ለልጆች በማስተላለፍ የእርስበርስ ፍቅርን፣ መተሳሰብን፣ አንድነትን፣ መከባበርን እና መቻቻልን የሚንፀባረቅበት ሲምፖዚየም ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ፈሰሰወርቅ አክለውም ከልዩነት ይልቅ አንድነትን፣ ከጥፋት ይልቅ ልማትን እንዲሁም የእርስበርስ መተሳሰርን በማጠናከር የጋራ ባህላዊ እሴቶችን ለትውዱ በማስተላለፍ ረገድ ሁሉም የብሔሩ ተወላጆች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም አስተላልፈዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *