የጉራጌ ማህበረሰብ ባህል ፣ታሪክ ፣ ቋንቋና ቅርስ በማልማትና በማሳደግ ማህበረሰቡ የሚመጥን ስራ ይሰራል ፦የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ

የጉራጌ የባህል፣ የቋንቋና የታሪክ ሲፖዚየም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት የጉራጌ ባህል ቋንቋ እና ቅርሶች እንዲለሙ እንዲተዋወቁ እና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ገልጸዋል።

የጉራጊኛ ቋንቋ ለማሳደግ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጀምሮ በአሁን ወቅት ሁለተኛ ክፍል ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይ ጉራጌን አንድ ሊያደርጉ የሚችሉ ስራዎች መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ላጫ የጉራጌ ሸንጎ ማጠናከር ፣የጋራ ምክር ቤት ማቋቋም፣ የጉራጌ ቴሌቬዥን ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግና ሌሎችም ጉራጌ የሚመጥኑ ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ጀፎረ ተጠብቆ እንዲቆይ እና ያለአግባብ እንዳይበላሽ መስራት እንደሚገባ የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው የጉራጌ ክትፎ በአለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ላጫ አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የዘንድሮ የጉራጌ ባህል ፣ቋንቋና የታሪክ ሲፖዚየም ባማረ መልኩ ተዘጋጅቶ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸው አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *