የጉራጌ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ከማሳደግ ባለፈ አንድነቱና አብሮነቱን ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።

የጉራጌ የባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚየም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል።

የጉራጌ ልማት ባህል ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ እንዳሉት ልማት ማህበሩ የጉራጌ ማህበረሰብ አንድነትና አብሮነት ይበልጥ እንዲጎለብት ከመስራት ባለፈ የማህበረሰቡ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ለማሳደግ ስራዎች እየሰራ ይገኛል።

የጉራጊኛ ቋንቋ ለማሳደግ በሚዲያና በትምህርት የተጀማመሩ ስራዎች ማስቀጠል እንደሚገባ ያነሱት አቶ ሺሰማ ልማት ማህበሩ የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

የጉራጌ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ከማሳደግ ባለፈ አንድነቱና አብሮነቱን ለማጎልበት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ጀፎረ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች እያካሄደ መሆኑን ጠቁመው ይህ ውብ ባህላዊ እሴት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው የጉራጌ ባህል ቋንቋና ታሪክ ለማሳደግ የተጀማመሩ ስራዎችን ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተው ለዚህም ዩኒቨርስቲው የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተናግረዋል።

ለዚህም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ለመክፈት በቀጣይ እንደሚሰራም አመላክተዋል።

የጉራጊኛ ቋንቋ ለማሳደግ በትምህትና በሚዲያ የተጀማመሩ ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥሉ ይገባል ያሉት ዶ/ር ፋሪስ የተጀማመሩ ስራዎች የሁለቱ ዞን አመራሮች በጀመሩት ልክ ማጠናከር እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

በመጨረሻም ሲምፖዚየሙ በዚህ ደረጃ እንዲካሄድ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች እንዳሉት ሲምፖዚየሙ በዚህ መልኩ መከበሩ መደሰታቸውን አንስተዋል።

የጉራጌ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ለማሳደግ መሰል ሲምፖዚየሞች መጠናከር ይኖርባቸዋል ያሉት ተሳታፊዎቹ ይህም ሳይበረዙ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *