የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ዘንድሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚከበረው 20ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል አስመልክቶ በኪነ ጥበብ
እና በስነ ምግባር ዙሪያ ለኪነት ቡድን አባላትና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ሰልጠና በወልቂጤ ከተማ መስጠት ጀመረ።
ስልጠኞች የሚሰጣቸውን ስልጠናው በአግባቡ በመከታተል በሚቀጥለው ወር የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በድምቀት እንዲከበር የተጣለባቸውን ድርብ ኃላፊነት እንዲወጡ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።
የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት የዘንድሮ የብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን ለ20ኛ ጊዜ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ከተሞች በተለይም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ጭምር በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልጸው ለዚህም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለሚመጡ እንግዶች የጉራጌ ብሄር የሚመጥን የእንግዳ አቀባበል እንዲያደርጉ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
በተለይም ኪነ ጥበብ የአንድነት ብሔር ማንነት፣ ትውፊትንና እሴትን አጉልቶ የሚያሲይ እንደመሆኑ መጠን በዘንድሮ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን የጉራጌ የባህል አምባሳደር የሆኑት የኪነት ቡድን አባላት የተጣለባቸውን ድርብ ኃላፊነትን እንዲወጡ ለማስቻል ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በጉራጌ የባህል ሴቶች፣ በውዝዋዜ፣ በድምጽ አወጣጥና በስነ ምግባር ዙሪያ መሰረታዊ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለተከታታይ 5 ቀናት የእቅድ ስልጣን እየተሰጠ እንደሆነ አብራርተዋል።
ስልጠኞች የሚሰጣቸውን ስልጠናው በአግባቡ በመከታተል ወደ ተግባር በመቀየር በሚቀጥለው ወር የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በድምቀት እንዲከበር የተጣለባቸውን ድርብ ኃላፊነት እንዲወጡ ሲሉ ተናግረዋል ።