የጉራጌ ቱባ ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ

የጉራጌ ቱባ ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩና እንዲተዋወቁ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለማጎልበትና ለማሸጋገር መሰነድና ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል።

በዞኑ ቋንቋና ቱባ ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩና እንዲተዋወቁ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ሲፖዚየም ጥናታዊ ጹሁፎች የቀረቡ ስለመሆኑ ያነሱት ወ/ሮ መሰረት የጉራጌ ክትፎ እና ሌሎችም በየደረጃቸው በአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ይሰራል ነው ያሉት።

የባህላዊ ዕሴቶች መጠናከር ለእርስ በርስ ትስስርና ለሀገር እድገት የሚያበረክተውን ፋይዳ እውን ለማድረግ መሰል የማስተዋወቅ ተግባራት እንደሚጠናከሩ አመላክተዋል።

በዞኑ እንደ ጀፎረ ያሉ ሀገር በቀል እውቀቶችና ባህላዊ እሴቶች እንዲለሙ፣ እንዲጠበቁና ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመዋል።

የጉራጌ የእደ ጥበብ ውጤቶችን በሲምፖዚየሙ ማስተዋወቅ መቻላቸውንና በዚህም ዜጎች የገበያ ትስስር እንደ ተፈጠረላቸው ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *